የዳይሬክቶረቱን ሥራ ማቀድ፣ ማስተባበር፣ መምራት፣ ማስፈፀሙን መከታተል ውጤቱን መገምገም፣

አገልግሎቶች

የዳይሬክቶረቱን ሥራ ማቀድ፣ ማስተባበር፣ መምራት፣ ማስፈፀሙን መከታተል ውጤቱን መገምገም፣

  • ከክልላዊ ዕቅድ የተመነዘረውን የኮሚሽኑን ስትራቴጂክ ዕቅድ መሠረት በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፡፡ ከቡድን አባላት ጋር በመወያየት ያዳብራል፣ ያፀድቃል ተግብራዊነቱንም ይከታተላል ግብረ-መልስ ይሰጣል፣
  • የዳይሬክተሩን የሥራ አፈፃፀም በየጊዜው ይገመግማል በየጊዜው የታዩ መልካም ለውጦችን በመፈተሸ የተገኘውን ውጤት ያመለክታል፣ የአባላቱን ውጤት ያሳውቃል፣
  • የዳይሬክቶሬቱ ዕቅድ መሠረት ባደረገ መልኩ ቡድኖች ዕቅዳቸውን እንዲቀርፁ ያደርጋል፤ ሥራዎችን ያከፋፍላል፣
  • በተገኘው የግምገማ ውጤት መሠረት በሚታዩ ችግሮች ላይ ቀጣይ አቅጣጫዎች ያመላክታ፤ ለቅርብ ኃላፊው ሪፖርት ያደርጋል፣
  • ዳይሬክቶሬቱ በበቂ የሰው ኃይልና የመገልገያ መሣሪያዎች መደራጀቱንና ትክክለኛ የሀብት አያያዝና አጠቃቀም መኖሩን ያረጋግጣል፣ ውሳኔ ለሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ወቅታዊ ምላሾችን ይሰጣል፣
  •  የቡድኖችን የአቅም ክፍተቶች በመለየት ለሥራው ብቁ ውጤታማና ቀልጣፋ ሊያደርጋቸው የሚያስችል ሥልጠና እንዲያገኙ ያደርጋል፣
  •  የቡድኖች የሥራ ዕቅድ በተመለከተ ከቡድን መሪዎች ጋር መግባባት ላይ ይደርሳል፣
  •  የዳይሬክቶሬቱን ባለሙያዎችና ሠራተኞች ዕውቀት ልምድና ችሎታቸውን ለሥራው ውጤት መጎልበት እንዲያውሉት ያበረታታል፣
  •  የዳይሬክቶሬቱን ሥራ ውጤታማ ለማድረግ የተቀየሱ አሠራሮች በተገቢው መንገድ መተግበራቸውን እና የሚፈለገው ውጤት እያመጡ መሆናቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣
  •  የቡድኖችን ሥራ አፈፃፀም በተዘጋጀው መለኪያ መሠረት ውጤቱን ይገመግማል፣ ከቡድን መሪዎች ጋር ተወያይቶ መግባባት ላይ ይደርሳል፣ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን ይለያል፣ ድክመቶች የሚታረሙበትንና ጠንካራ ጎን የሚጎለብትበትን መንገድ ያመቻቻል፣
  •  በቡድኖች እንዲሁም በሥራ ባልደረቦች መካከል ተፈላጊውን የሥራ ግንኙነትና ቅንጅት እንዲኖር ያደርጋል፣ ልዩነቶች/ችግሮች/ ሲኖሩ መፍትሔ በመስጠት ጥሩ የሥራ ግንኙነት ይፈጥራል፣
  •  በዳይሬክቶሬቱ ባልደረቦች መካከል የልምድ ልውውጥ እንዲኖር ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ የዳይሬክቶሬቱ ባልደረቦች ከሌሎች ተቋማት ጋር የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ ያደርጋል፣
  •  የዳይሬክቶሬቱን ባልደረቦች ተግባራቸውን በመልካም ሥነ-ምግባር እንዲፈፀሙ ያደርጋል፣ ድጋፍ ይሰጣል፣ ጉድለት የፈፀሙትን ደግሞ ተጠያቂ ያደርጋል፣

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *