የክልሉ የሥነ-ምግርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ በአሶሳ ዞን ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለተደራጁ የተማሪዎች የሥነ-ምግባር ክበባት በጋራ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
የድጋፉ አላማ የፀረ-ሙስና ትግሉን ማሳለጥ ሲሆን ትኩረቱን በተማሪዎች ሥነ-ምግባር ክበብ አደረጃጀትና አሰራር ላይ አድርጓል፡፡
በዚህ ክትትልና ድጋፍ የሁለቱን ተቋማት ባለሙያዎች ጨምሮ ሲቪክ ማህበራት በቅንጅት ተሳትፈውበታል፡፡
