ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ.ር አብይ አህመድ ከወጣቶች ጋር ባደረጉት ውይይት ሌብነትን በሚመለከት ከተናገሩት፤

ወቅታዊ መረጃ
ሌብነት በጣም እያስቸገረን ያለ በሽታ ነው፡፡ ነገር ግን መገንዘብ ያለብን ነገር ሰው በሌብነት ልብሱን ሊቀይር ይችላል፤ የልጁን ምግብ ሊቀይር ይችላል፤ ሳሎን ሊቀይር ይችላል፤ ቤት ግን አይገነባም ፡፡ ቤት ሰርቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ሃገር መስራት እስካልቻለ ድረስ ግን ያ ቤት ይፈርሳል ፤ ይወረሳል፡፡ ይሄ ብዙ ፍልስፍና አያስፈልገውም በባለፈው ብዙ ቦታ፣ ብዙ ፎቅ የሰሩ ግለሰቦች አሁን አይኖሩበትም ፡፡ እናም ሌብነት ሳሎን ቢገነባ ቤት አይገነባም፣ ቤት ቢገነባ ሃገር አይገነባም፣ ሃገር ከሌለ ደግሞ ቤት ብቻውን አይቆምም፡፡
የሌብነት ችግር አለ ፤ በቅርቡ ትሰማላችሁ ስራ ጀምረናል፡፡ በቀጣይ ‘አግሬሲቭሊ’ ከምንሰራበት አንዱ ሌብነት ነው ፡፡ ማን ላይ እንደሚያርፍ አላውቅም ማንም ላይ ቢያርፍ ግን ጠንከር ያሉ ስራዎች ይሰራሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *