ኮሚሽኑ ለመከታተያ ክፍሎች እያደረገ ያለው ዘርፈ ብዙ እገዛ የመከታተያ ክፍሎች ስራቸውን ተረጋግተው እንዲሰሩና በፀረ-ሙስና ትግሉ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የሚያግዝ መሆኑ ተገለፀ፡፡ *******************

ወቅታዊ መረጃ
በሸርቆሌ ወረዳ የኢኮኖሚ ዘርፍ የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያ አቶ አልታሰብ ቢሌ በአዲሱ የበጀት አመት አመርቂ የሙስና መከላከል ስራዎችን ለመስራት የሚያስችላቸውን የዕቅድ ማናበብና ለስራቸው መሳሪያ የሚሆናቸውን ስልጠናዎች መውሰዳቸውን ከስራ ክፍላችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል፡፡ በተያዘው የበጀት አመትም ከኮሚሽኑ ዕቅድ ጋር በሚጣጣም መልኩ አቅደው ወደ ስራ መግባታቸውን አቶ አልታሰብ ቢሌ ተናግረዋል፡፡
ከስልጠና ባለፈም ኮሚሽኑ ለስራችን ስኬታማነት ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ከወረዳ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት መስራት መጀመሩ የሚበረታታ ለእኛም የሥራ ተነሳሽነት የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡
ችግሮቻችን በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰሚ እያገኙና እየተፈቱ ነው ያሉት ባለሙያው የሥራ ክፍሉ የፀረ-ሙስና ትግሉን ለማሳለጥ የበጀት አርዕስት የሌለው መሆኑ ግን ዛሬም ለስራቸው እንቅፋት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ይህም የሥራ ክፍሉ የሙስና መከላከል ስራዎችን በሌሎች መልካም ፍቃድ እንዲሰራ በማድረግ አሉታዊ ተፅእኖ እንዳለው አስረድተዋል፡፡ ችግሩን ለመፍታት ኮሚሽኑ ከወረዳ ባለድርሻ አካላትና አመራሮች ጋር በተደጋጋሚ መነጋገሩንና በደብዳቤ ጭምር መጠየቁን አስታውሰው ችግሩን ለመፍታት የተሄደበትን እርቀት አድንቀዋል፡፡
አሁንም ኮሚሽኑ ችግሩ እንዲፈታ የተቻለውን ሁሉ በማድረግ ግፊቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል አቶ አልታሰብ ቢሌ ጠይቀዋል፡፡
May be an image of 1 person and indoor
You, Mengistu Lalo, Meseret Girmay and 10 others

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *