ሌቦች አንገታቸውን ቀና አድርገው የሚሄዱበት ንፁሃንና እውነትን የተከተሉ የሚሸማቀቁበት ሃገር ልትኖረን አይገባም፡፡ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

- ወቅታዊ መረጃ
ሌቦች አንገታቸውን ቀና አድርገው የሚሄዱበት ንፁሃንና እውነትን
የተከተሉ የሚሸማቀቁበት ሃገር ልትኖረን አይገባም፡፡
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
“ሙስና ላይ ለምናደርገው ትግል ትልቅ ጉልበት የሚሆን የምስራች ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ብሄራዊ ኮሚቴ በማቋቋም አሰምተውናል ፤ ይህንን እድል እንጠቀምበት!!
አዎ ! ሙስና ሀገርና ትውልድ የሚገድል ነቀርሳ ነው፡፡ የሀገርንና የህዝብን ሀብት ከሌቦች ለመታደግ በምናደርገው ትግል ሌቦች አንገታቸውን ቀና አድርገው የሚሄዱበት ንፁሃንና እውነትን የተከተሉ የሚሸማቀቁበት ሃገር ልትኖረን አይገባም፡፡
ትግሉን ማቀጣጠል ይገባናል፡፡ በየመድረኩ ሙስና እንቅፋት ሆነብን ብሎ ለሚወቅሰው አመራርም ይሁን ህዝብ ይህ ትልቅ እድል ነው፡፡ እድሉን ሲገኝ ደግሞ ያለ አንዳች ፍርሀት እና ይሉኝታ በሚገባ መጠቀም ይኖብናል።
ይህ ካልሆነ ነቀርሳው ካንዱ ወደ ሌላው እየተላለፈ ትውልድ እና ሀገር ይገድላል።
ስለዚህ መረጃ እና ማስረጃ ያለው ፤ በተለይም የአዲስ አበባ ነዋሪና ሙስናን ለመታገል ጥረት የምታደርጉ አመራሮች ፤ ሰራተኞች ሁሉ ተገቢውን መረጃና ማስረጃ ዛሬ ለተዋቀረው ለብሄራዊ ኮሚቴ በማቅረብ ሃገራዊ ኃላፊነታችንን እንድንወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ!!”
 ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *