ኮሚሽኑ ድጋፍ ለሚሹ 13 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች 13350 ብር የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ፤ ድጋፍ ለሚሹ 13 ተማሪዎች ለግሰዋል፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ነጅመዲን አልመሃዲ ድጋፉን ባበረከቱበት ወቅት እንዳሉት ተማሪዎች በስነ-ምግባራቸው የተመሰገኑ፣ በትምህርታቸው ጠንካራ መሆን እንደሚገባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ይህን ሰናይ ተግባርም ተቋሙ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡ የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች 13 ተማሪዎችን በየአመቱ በቋሚነት እንደሚደግፉ የሚታወቅ ነው፡፡
ተጨማሪ ያነቡ