ኮሚሽኑ የሐብት ማስመዝገብና ማሳወቅ መረጃዎች ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ፣ ወጭና ጊዜን ሊቆጥብ በሚችል መልኩ መያዝ የሚያስችለውን የመረጃ አያያዝ ሥርዓት ከክልሉ ሳይስና ቴክኖሎጅ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ሲያስለማ መቆየቱን የገለፁት በኮሚሽኑ የሐብት ማስመዝገብና ማሳወቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ወዲሻ ናቸው፡፡
ይህም ውጤታማ የሙስና መከላከል ስራዎችን በመስራት ረገድ የሐብት ምዝገባ መረጃዎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና ቀልጣፋ አሰራር ለመዘርጋት እንደሚያስችል ዳይሬክሩ ጠቁመዋል፡፡
የመረጃ አያያዝ ስርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግም ለዘርፉ ቅርብ ለሆኑ ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ ስልጠናውን የሚሠጡት በክልሉ የሳይንስና ቴክኖሎጅ ኤጀንሲ የሶፍትዌር ባለሙያ አቶ ቢኒያም ተፈራ ናቸው ፡፡

