ሙያዊ ሥነ-ምግባርን በመላበስ  ህብረተሰቡ የሚፈልገውን አገልግሎት  መስጠት ይገባል –  አቶ አለም ደበሎ

ወቅታዊ መረጃ

 

ሙያዊ ሥነ-ምግባርን በመላበስ፤ ህብረተሰቡ የሚፈልገውን  አገልግሎት በማድረስ ይገባል፡፡ ይህን ስናደርግ ሙስናና ብልሹ አሰራር  በተቋምና በሃገር ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ኪሳራ ቀድመን  መከላከል እንችላለን፡፡

 

በዚህ ረገድ የተቋሙ ሰራተኞች ሙያዊና የዜግነት ግዴታቸውን አበክረው  እንዲወጡ  የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት  ጤና ቢሮ ም/ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለም ደበሎ ተናግረዋል፡፡

 

ም/ቢሮ ኃላፊው ይህን ያሉት የክልሉ ጤና ቢሮና ተጠሪ ተቋማት አመራችና  ሰራተኞች 22 ኛውን የአለም የፀረ-ሙስና ቀን “ትውልድን በሥነ-ምግባር ተቋምን በአሰራር!” በሚል መሪ ቃል   በፓናል ውይይት ባከበሩበት ወቅት ነው፡፡

 

መሪ ቃሉን መነሻ በማድረግ ሰነድ ያቀረቡት   የቢሮው የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ባለሙያ አቶ ሃምሳ አለቃ ቶለሳ፤ ሰራተኞች በተመደቡበት የሙያ መስክ የተቋሙን አሰራር በመጠበቅ አገልግሎት ሊሰጡ  እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

 

አቶ ሃምሳ አለቃ ግልጽነት የጎደለላቸውን አሰራሮች ማሻሻልና   ለሙስናና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ የአሰራር ሂቶችን መዝጋት እንደሚገባም  አስረድተዋል፡፡ አሰራሮችን  ከሙስናና ብልሹ አሰራር ለመከላከልም የሁሉም አካላት ተሳትፎና እርብርብ እንዲሚስፈልግ አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

 

በዚህ መድረክ ግልፅነት የሚሹ ጥያቄዎችና አስተያዬቶች ከተሳታፊዎች የተነሱ ሲሆን ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷባቸው የጋራ ግንዛቤ ተይዟል፡፡

 

22ኛው የአለም የፀረ-ሙስና ቀን በክልል በሚገኙ የተለያዩ የመንግስት ተቋማት መከበሩን ቀጥሏል፡፡

 

ከክልሉ ጤና ቢሮ የማህበራዊ ትስስር ገፅ፤  ለገጻችን እንዲያመች ተደርጎ የተወሰደ፤

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *