ዕውቀት፣  አቅምና ችሎታ   በስነ-ምግባር ካልተመራ ትርጉም የለውም  –  አቶ ንጋቱ ጌታሁን

ወቅታዊ መረጃ

 

 

ለገመሃሮ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የስብዕናና የሞራል እሴቶች ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የኮሚሽኑ የፊት ለፊት የሥነ-ምግባር ትምህርትና ሥልጠና ባለሙያ  አቶ ንጋቱ ጌታሁን ተማሪዎች ከመደበኛው ትምህርት ጎን ለጎን ከፍ ያለ ስብእናና ሞራልን ሊገነቡ እንደሚገባ ገልፀው፤ መልካም ሥነ-ምግባር ዓለማቸውን ለማሳካትም አንዱና ዋነኛው መሳሪያ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

 

ባለሙያው አክለውም ምንም ያህል ዕውቀትና ችሎታ  ብንጎናፀፍ እንኳን  በስነ-ምግባር ካልተመራ ትርጉም የለውም ነው ያሉት፡፡

በዚህ ስልጠና ከ300 በላይ ተማሪዎች ስልጠናውን ወስደዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *