
ለዳን ዲ ቦሩ ኮሌጅ አሶሳ ካምፓስ ተማሪዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የኮሚሽኑ የፊት ለፊት የሥነ-ምግባር ትምህርት ስልጠና ባለሙያ አቶ ንጋቱ ጌታሁን የነገይቱን ኢትዮጵያ በመሪነት የሚያገለግሉ፣ በህክምናው ዘርፍ ታማሚዎችን የሚያግዙ፣ በግንባታው ዘርፍ ድንቅ ህንፃዎችን የሚሰሩ፤ በተለያዩ ዘርፎች ውጤታማ ዜጎች የሚገኙትና የሚጠበቁት ከዛሬዎቹ ወጣቶች መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ሐገርና ሕዝብ የሚሰጠውን ኃላፊነትና አደራ በብቃት ለመወጣትም በሥነ-ምግባር መታነፅና በእውቀት መጎልበት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ወጣቶች አበክረው መዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት አቶ ንጋቱ ፡፡
ኮሚሽኑ ትውልዱን በሥነ-ምግባር ለማነፅ የሥብዕናና የሞራል እሴቶች ግንባታ ስራውን አጠናክሮ መስራቱን ቀጥሏል፡፡
