የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች ድፍረት የተሞላበትና የማያቋርጥ የፀረ-ሙስና ትግል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ

(አሶሳ፤ ነሐሴ 20/2014 ዓ.ም) የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች ድፍረት የተሞላበትና የማያቋርጥ የፀረ-ሙስና ትግል ማድረግ እንደሚገባቸው ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ አሳሰቡ፡፡ የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች ሙስናን በመከላከል ረገድ ባሳለፍነው የበጀት አመት የነበራቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተቋማት የሥራ ኃላፊዎችና አመራሮች የመከታተያ ክፍሎችን እንደ አንድ የሥራ አጋር መቁጠር መጀመራቸውና በመመካከር ስራ ለመስራት የሚያደርጉት ጥረትም ለዚህ አንዱ ማሳያ […]

ተጨማሪ ያነቡ

«የክልሉን መሪ ዕቅድ ወደ ተቋም በመቀየር በተቋምም ሆነ በየደረጃ ላሉ ፈጻሚ አካላት ግንዛቤ በመፍጠር ለተፈጻሚነቱ በሙሉ አቅማቸው እዲዘጋጁ የሚደረግ ይሆናል›› ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ

(አሶሳ÷ ነሃሴ 3/2014 ዓ.ም ) የቤኒሻንጉል ጉ/ክ/ሥነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን የስራ – አመራር ኮሚቴ በ2015ዓ/ም ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱ ኮሚሽኑ የ2015 ዓ.ም መሪ ዕቅድ ሙስና እና ብልሹ አሰራርን ውጤታማ በሆነ መልኩ በመከላከል የህዝብና የመንግስትን ሃብት ከምዝበራ ፣ ከስርቆት እና ከብክነት ለማዳን በሚያስችል መልኩ መዘጋጀቱንና በበጀት አመቱ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሰራ በውይይቱ ተገልፆል::

ተጨማሪ ያነቡ

ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ.ር አብይ አህመድ ከወጣቶች ጋር ባደረጉት ውይይት ሌብነትን በሚመለከት ከተናገሩት፤

ሌብነት በጣም እያስቸገረን ያለ በሽታ ነው፡፡ ነገር ግን መገንዘብ ያለብን ነገር ሰው በሌብነት ልብሱን ሊቀይር ይችላል፤ የልጁን ምግብ ሊቀይር ይችላል፤ ሳሎን ሊቀይር ይችላል፤ ቤት ግን አይገነባም ፡፡ ቤት ሰርቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ሃገር መስራት እስካልቻለ ድረስ ግን ያ ቤት ይፈርሳል ፤ ይወረሳል፡፡ ይሄ ብዙ ፍልስፍና አያስፈልገውም በባለፈው ብዙ ቦታ፣ ብዙ ፎቅ የሰሩ ግለሰቦች አሁን አይኖሩበትም ፡፡ […]

ተጨማሪ ያነቡ

የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች የሙስና መከላከል ስራዎችን ውጤታማነት ለማሳደግ በሚያስችለው የ2015 የበጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ተወያዩ፡፡

(አሶሳ፤ ሐምሌ 14 /2014) የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች በ2015 የበጀት ዓመት የሙስና መከላከል ሥራዎችን በተሻለ መልኩ ለመፈፀም ይረዳ ዘንድ በበጀት አመቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ዕቅድ ቀርቦ ሁለት ቀናት የወሰደ ውይይት በኮሚሽነሩ ጽ/ቤት ተደርጓበታል፡፡ ኮሚሽኑ በበጀት አመቱ አስቸኳይ የሙስና መከላከል ስራዎች (በስነ-ምግባር እሴቶች ግንባታ ፣ የአውታሮች አደረጃጀትና የአሰራር ጥናት) ፣ የሀብት ምዝገባ እና ማጣራት […]

ተጨማሪ ያነቡ

የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች በአረንጓዴ አሸራ መርሃ ግብር በአምባ አስራ አንድ ቀበሌ ከ200 በላይ የማንጎ ችግኞችን ተከሉ፡፡

(አሶሳ፣ ሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም) የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች እንደ ክልል እና እንደ ሃገር የተያዘውን የአረንጓዴ አሸራ መርሃ ግብር የሚያግዝ የችግኝ ተከላ በአምባ አስራ አንድ ዳቡስ ተፋሰስ 240 የማንጎ ችግኞችን በመትከል አካሄዱ፡፡ ክልሉ በተያዘውና በአራተኛው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አሻራችን ለትውልዳችን በሚል መሪ ቃል ከ 7.5 ሚሊዬን በላይ ችግኞችን በአንድ ጀምበር ለመትከል አቅዶ በመስራት ላይ […]

ተጨማሪ ያነቡ

በንግዱ ዘርፍ የሚስተዋለው ብልሹ አሰራር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመምጣቱ በህብረተሰቡ ውስጥ ከፍተኛ ምሬት እያመጣ በመሆኑ አስቸኳይ እና ወቅታዊ ምላሽ መስጠት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ….፡፡

የቤኒሻንጉል /ጉ/ክ/ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በአሶሳ ከተማ ከሚገኙ የንግድ ማህበረሰብ ጋር ውይይት አካሄደ፡፡ የውይይቱ መነሻ ሀሳብ የነበረው ‹‹ በንግዱ ዘርፍ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራር ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው›› የተመለከተ በስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተሰራው የዳሰሳ ጥናት ቀርቧል፡፡ የመድረኩ አላማ በንግድ ዘርፍ የሚስተዋለውን ብልሹ አሰራር እና እያስከተለ ያለውን ችግር ነቅሶ ለማውጣት ከባለድርሻ አካላት ጋር መወያየቱ የተሻለ […]

ተጨማሪ ያነቡ

ኮሚሽኑ በአሶሳ ዞን የሚሰሩ የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች ጋር ውይይት አደረገ፡፡

ኮሚሽኑ በአሶሳ ዞን የሚሰሩ የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች የ100 ቀን እቅድ አቅደው ሊተገብሩ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ውይይት አደረገ፡፡

ተጨማሪ ያነቡ

ለህዝብ አገልግሎት ታስበው የሚሰሩ የግንባታ ፕሮጀክቶች ጥራታቸውን የጠበቁና ከብልሹ አሰራር የፀዱ መሆን እንዳለባቸው ኮሚሽነር መንግስቱ ላሎ አሳሰቡ፡፡

ኮሚሽነሩ ይህን ያሉት ከክልሉ የመሰረተ ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በአሶሳ ከተማ አስተዳደር በ UIIDP የገንዘብ ድጋፍ የሚሰሩ መሰረተ ልማቶች ያሉበትን ደረጃ ክትትል ባደረጉበት ጊዜ ነው፡፡

ተጨማሪ ያነቡ

በክልሉ የሚስተዋሉ ለኑሮ ውድነት አባባሽ የሆኑ መንስኤዎችን በአጭር ጊዜ ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ከመንገድ ትራንስፖርት፣ ከንግድና ከፍትህ አካላት የተዋቀረው ግብረ-ኃይል አስታወቀ፡፡

በትራንስፓርት እና በንግዱ ዘርፍ የሚስተዋለው የተጋነነ ክፍያ ከጊዜ ወደ ጊዜ መባባሱን ቀጥሏል፡፡ ለማህበረሰቡም ኑሮን ለመግፋት ትልቁ ፈተና ሁኖ ዘልቋል፡፡ ችግሩን ለመፍታትም መንግስት ከማህበረሰቡ ጋር ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡ በየደረጃው የሚገኘው አመራር የኑሮ ጫናውን ሊያቀሉ የሚችሉ እርምጃዎች እንዲወሰዱ አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡ በቅርቡም የፍትህ አካላትን፣ በትራንስስፖርትና በንግዱ ዘርፍ የሚሰሩ ኃላፊዎችና አመራሮችን የያዘ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ ግብረ […]

ተጨማሪ ያነቡ

የክልሉ የሥነ-ምግርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ በአሶሳ ዞን ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለተደራጁ የተማሪዎች የሥነ-ምግባር ክበባት በጋራ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ የድጋፉ አላማ የፀረ-ሙስና ትግሉን ማሳለጥ ሲሆን ትኩረቱን በተማሪዎች ሥነ-ምግባር ክበብ አደረጃጀትና አሰራር ላይ አድርጓል፡፡ በዚህ ክትትልና ድጋፍ የሁለቱን ተቋማት ባለሙያዎች ጨምሮ ሲቪክ ማህበራት በቅንጅት ተሳትፈውበታል፡፡

ተጨማሪ ያነቡ