አንድ ትውልድ ትውልዳዊ ፍሰቱን ጠብቆ  በስኬት መጓዝ ይችል ዘንድ፤  ሃገራት ከቁሳዊ ሥልጣኔ  ባሻገር በመንፈስ የሰለጠነ፤ በሥነ – ምግባር የታነፀና ባለራዕይ ዜጋ ያስፈልጋቸዋል – አቶ አወቀ ገ/መስቀል

ለሚሊነዬም ኮሌጅ አሶሳ ካምፓስ ተማሪዎች የስብዕናና የሞራል እሴቶች ግንባታ በሚል ይዘት  የግንዛቤ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡   ስልጠናውን  የሰጡት የኮሚሽኑ  የፊት ለፊት የሥነ-ምግባር ትምህርትና ስልጠና ባለሙያ አቶ አወቀ ገ/መስቀል  አንድ ትውልድ ትውልዳዊ ፍሰቱን ጠብቆ  በስኬት መጓዝ ይችል ዘንድ፤  ሃገራት ከቁሳዊ ሥልጣኔ  ባሻገር በመንፈስ የሰለጠነ፤ በሥነ – ምግባር የታነፀና ባለራዕይ ዜጋ ያስፈልጋቸዋል ፡፡  ወጣቱም እራሱን በዚሁ ልክ ማዘጋጀት […]

ተጨማሪ ያነቡ

ኮሚሽኑ  ለኤም ኤ ኮሌጅ አሶሳ ካምፓስ ተማሪዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

  ስልጠናው የተማሪዎችን ስብዕና በመገንባት፣ በተለይም ተማሪዎች ከኮሌጅ ትምህርት በኋላ በሚሰማሩበት የስራ መስክ፤ ለማህበረሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለማድረስ እንደሚያስችል ስልጠናውን የሰጡት የኮሚሽኑ የፊት ለፊት የሥነ-ምግባር ትምህርትና ስልጠና ባለሙያ አቶ ንጋቱ ጌታሁን ገልፀዋል፡፡   የመልካም ስብዕና ባለቤት መሆንም  የራስን ዓለማና ራእይ ለማሳካትና  በህይወት ስኬትን ለመጎናፀፍ እንደሚያግዝ፣ ከዚህ ሲያልፍም ለማህበረሰብና ለሃገር ሁለንተናዊ እድገት ሚናው  የላቀ መሆኑን አሰልጣኙ አስገንዝበዋል፡፡

ተጨማሪ ያነቡ

ዕውቀት፣  አቅምና ችሎታ   በስነ-ምግባር ካልተመራ ትርጉም የለውም  –  አቶ ንጋቱ ጌታሁን

    ለገመሃሮ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የስብዕናና የሞራል እሴቶች ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ስልጠናውን የሰጡት የኮሚሽኑ የፊት ለፊት የሥነ-ምግባር ትምህርትና ሥልጠና ባለሙያ  አቶ ንጋቱ ጌታሁን ተማሪዎች ከመደበኛው ትምህርት ጎን ለጎን ከፍ ያለ ስብእናና ሞራልን ሊገነቡ እንደሚገባ ገልፀው፤ መልካም ሥነ-ምግባር ዓለማቸውን ለማሳካትም አንዱና ዋነኛው መሳሪያ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡   ባለሙያው አክለውም ምንም ያህል ዕውቀትና ችሎታ  ብንጎናፀፍ እንኳን  በስነ-ምግባር […]

ተጨማሪ ያነቡ

ወጣቶች እራሳቸውን በሥነ-ምግባር በመግራት ህይወታቸውን በምክንያታዊነት መምራት ይገባቸዋል – አቶ  አወቀ ገ/መስቀል

የተማሪዎችን ስብዕና መገንባት አላማ ያደረገ ሥልጠና ለብራይት ሜዲካል ኮሌጅ አሶሳ ካምፓስ ተማሪዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡   ወጣቶች እራሳቸውን በሥነ-ምግባር በመግራት እና እራሳቸውን በመቆጣጠር ሕይወታቸውን በምክንያታዊነት መምራት እንደሚጠበቅባቸው የኮሚሽኑ የፊት ለፊት የሥነ-ምግባር ትምህርትና ስልጠና ባለሙያ አቶ አወቀ ገ/መስቀል ትምህርቱን  በሰጡበት ወቅት ተናግረዋል፡፡   የህክምና ሙያ በጥብቅ ሥነ-ምግባር መመራት አለበት ያሉት   አቶ አወቀ ተማሪዎች  በቀጣይ ወደ ስራው  አለም […]

ተጨማሪ ያነቡ

ለራሳችሁ የምትመኙትን ለሌሎችም እንዲሆን እስካልተመኛችሁ ድረስ በትክክል አላመናችሁም (የነብዩ መሐመድ ተግባራትና ንግግሮች ) እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተም ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው ህግም ነቢያትም ይህ ነዉና (ክርስትና / ማቴ 7፣12) ሥለዚህ ወጣቶች እለት በእለት በሚያደርጉት ማህበራዊ መስተጋብር ውስጥ ወርቃማ ግብረገባዊ ህጎች (Golden rules of morality) መጠበቅ ይገባቸዋል፡፡ አሁን ባለንበት ዘመን በወጣቶች ለሚስተዋሉ የሥነ-ምግባር ግድፈቶች የቴክኖሎጂና […]

ተጨማሪ ያነቡ

የወጣቶች ፤ የመልካም ሥነ-ምግባር ባለቤት መሆን ፤ በዘላቂ ሕይወታቸው ደስተኛና የተሻለ የኑሮ ዘይቤ እንዲኖሩ ያስችላል – አቶ ንጋቱ ጌታሁን

ለአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተማሪዎች ወጣትነትና ሥነ-ምግባር በሚል ርዕስ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ስልጠናውን የሰጡት የኮሚሽኑ የፊት ለፊት የሥነ-ምግባር ትምህርትና ስልጠና ባለሙያ አቶ ንጋቱ ጌታሁን የሥልጠናው ዓላማ ወጣቱ መልካምና እኩይ እሴቶችን ለይቶ ትክክለኛውን መንገድ ማሳየት፤ መልካም ስነ-ምግባርን ለሌሎች ማሻገር መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የወጣቶች የመልካም ሥነ-ምግባር ባለቤት መሆንም፤ በዘላቂ ሕይወታቸው ደስተኛና የተሻለ የኑሮ ዘይቤ ለመኖር እንደሚያስችላቸው ነው፤ ባለሙያው ያስገነዘቡት፡፡ […]

ተጨማሪ ያነቡ

በህዝባዊ ውይይት የሚነሱ የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አመራሩ በአግባቡ በመለየት፣ በመፍጠር እና በመፍጠን መርህ መመለስ ይገባል !! ፦ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ይህንን ከአሶሳ ከተማ አስተዳደር አጠቃላይ አመራሮች ጋር “የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግሥት ትሩፋቶች !!” በሚል መሪ ሐሳብ በአሶሳ ከተማ በተደረገው የህዝባዊ ውይይት መድረክ ላይ ህብረተሰቡ ባነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ዙሪያ ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡ በህዝባዊ ውይይት የሚነሱ የሰላም፣ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አመራሩ በአግባቡ በመለየት፣ በመፍጠር […]

ተጨማሪ ያነቡ

የሰነድ ማረጋገጫንና የምዝገባ አገልግሎትን ዲጂታላይዝድ በማድረግ ተገልጋዩን ከእንግልት ለማስቀረት እየተሰራ ነው

የሰነድ ማረጋገጫንና የምዝገባ አገልግሎትን ዲጂታላይዝድ በማድረግ ተገልጋዩን ከእንግልት ለማስቀረት እየተሰራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አስካለች አልቦሮ አስታወቁ። የክልሉ ፍትህ ቢሮ DARS ቴክኖሎጂ የኦንላይን አገልግሎትን በይፋ አስጀምሯል። ‎ ‎በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አስካለች አልቦሮ እንዳሉት በክልሉ ሲሰጥ የቆየው የሰነድ ማረጋገጥ አገልግሎት ደህንነቱን ባልጠበቀ መልኩ ሲስራ መቆየቱን አስታውሰዋል። ‎ […]

ተጨማሪ ያነቡ

በተቋማዊ እና ብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ የማይደራደሩ ታማኝ አገልጋዮች ያስፈልጉናል፡- ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር)

በተቋማዊ እና ብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ የማይደራደሩ ታማኝ አገልጋዮች፣ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞች እና የተቋማት ተገልጋዮች ያስፈልጉናል ሲሉ የፊዴራል የሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) ተናገሩ።   22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን ማጠቃለያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት እየተካሄደ ነው።   ከለውጡ ወዲህ የፀረ-ሙስና ትግል ጉድለትን የሚያርሙ ሥራዎች መሠራታቸውን እና ሕጎችን ማሻሻል […]

ተጨማሪ ያነቡ

በኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ውስጥ ሙስናን የሚጸየፍ ትውልድ መገንባት የሁሉም ድርሻ ሊሆን ይገባል –  ወ/ሮ አስካለች አልቦሮ

    ‎ ‎(አሶሳ፣ ኅዳር 26/2018 ዓ/ም) ሙስናን የሚጸየፍ ትውልድ በመገንባት የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ የሁሉም ድርሻ ሊሆን እንደሚገባ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አስካለች አልቦሮ ገለጹ። ‎ ‎በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል “ትውልድን በስነ-ምግባር፣ ተቋምን በአሰራር” በሚል መሪ ቃል በዓለማቀፍ ደረጃ 22ኛው፣ በኢትዮጵያ ደግሞ 21ኛው የጸረ-ሙስና ቀን በክልል ደረጃ ዛሬ በፓናል ውይይት ተከብሯል። ‎ በመድረኩ […]

ተጨማሪ ያነቡ